መጋቢት 23//2018 ዓ/ም
አሶሳ፣
በአሶሳ ከተማ አስተዳደር መሶብ የአንድ መረጃ ማእከል ክቡር ኘሬዝደንት አሻድሊ ሀሰንና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የአሶሳ ከተማ አስተዳደር አመራሮች በተገኙበት ተመርቋል።
በምረቃ መረሃ ግብር ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አብዱልከሪም አብዱራሂም በአሶሳ ከተማ መሶብ የአንድ መረጃ ማእከል መጀመሩ የአገልግሎት ችግርን ለመቅረፍ፣ጊዜና ሃይል ለመቆጠብ፣አገልግሎት ለማቀላጠፍ፣የመልካም አስተዳደር ችግር ለመቅረፍ
ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜና የተንከባለሉ ችግሮችን ለመቅረፍ መንግስት ትኩረት ካደረገባቸው ጉዳዮች የከተማና የገጠር ኮሪደር ልማት፣መኣድ ማጋራት፣ የስንዴ ልማት ፣አረንጓዴ አሻራ፣የሌማት ትሩፋት መስኮች መንግስት ባለው የመልማት አቅም በእነዚህ ዘርፎች ውጤት መመዝገቡን የክልሉ ርእሰ መስተዳደድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገልጸዋል።
በዛሬው እለት በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው መሶብ የአንድ መረጃ ማእከል ህዝቡ ሲያነሳ የነበረውን የአገልግሎት ችግር፣ብልሹ አሰራር ፣ የመልካም አስተዳደር ችግር ለመቅረፍ እና ዲጂታል ኢትዮጽያን እውን ለማድረግ ያግዛል ብለዋል ርእሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን።
አሁን የተጀመረውን አገልግሎት በማስፋፋት ጥራት ያለው አገልግሎት ለተገልጋዩ እንዲሰጥ ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻዲሊ ሀሰን አደራም ብለዋል።

