የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ሰልጣንና ተግባራቸዉን እንደገና ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 94/2003 መሠረት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የተሰጠዉ ተግባርና ኃላፊነት እንደሚከተለዉ ቀርቧል፡፡
- የከተማዉን የልማት ዕቅድና ስትራቴጂ ላይ የተመሰረተና በከተማ አስተዳደሩ የሚፈጸም የረዥም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ የልማት እቅድ ያዘጋጃል፣ ሲጸድቅም ተግባራዊነቱን ይከታተላል፡፡
- ከሚመለከታቸው የከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በረዥም በመካከለኛና በአጭር ጊዜ ዕቅዶች ውስጥ የሚንፀባረቁ በከተማ አስተዳደር የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች እንዲጠኑና እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ይከታተላል፣ ይገመግማል፡፡
- የየሴክተሩን እቅድ አፈጻጸም እየተከታተለና እየገመገመ የተቀነባበረ ሪፖርት በየሶስት ወሩ ለከተማ አስ/ር መንግስት ካቢኔ ያቀርባል፣
- የከተማ አስተዳደር አካላት የክልሉን የፋይናንስ ፖሊሲዎችን፣ህጐችን፣ደንቦችንና መመሪያዎችን ተከትለው መሰራታቸውን ይከታተላል ይቆጣጠራል፣
- ከተማ አስተዳደሩ የፋይናንስ ክንውን ይዞታና አስተዳደር የሚያስረዳ ጠቅላላ መግለጫ በየ 6 ወሩ ለከተማ አስተዳደር ካቢኔ ያቀርባል፡፡ ለአመቱ ከተዘጋጀው በጀት ሌላ ተጨማሪ በጀት ሲገኝና በተገቢው አካል ሲፈቀድ አዘጋጅቶ ያቀርባል፡፡
- ስለ ከተማዉ የፋይናንስ አያያዝና አጠቃቀም ጥናት እያደረገ የመፍትሄ ሃሳብ ያመነጫል፣
- የከተማ አስተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶችና ሁለቱን ወረዳዎች ጨምሮ የሚቀርቡትን መደበኛና የካፒታል በጀት ትክክለኛነት እየመረመረ ዓመታዊ በጀት አጠቃሎ በማዘጋጀት ለከተማ አስተዳድር ም/ቤት ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ያስተዳድራል፡፡
- የከተማ አስተዳድሩን መ/ቤቶች ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ መሰረት በማድረግ እንድተገብሩ ያደርጋል ፣ ተግባራዊነቱንም ይቆጣጠራል፡፡
- የከተማውን ህዝብ ልማት በበላይነት ይመራል፣ያስተባብራል፣ይከታተላል፣ ይገመግማል፡፡
- በክልሉ ገ/ኢ/ል/ቢሮ አማካኝነት ለከተማ አስ/ሩ ውስጥ ለመሥራት ፍላጐት ላላቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግና መረጃ በማቅረብ እንዲሁም የሚያቀርቡትን የልማት ዕቅድ በማቀድ ያስተባብርል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ ይገመግማል፡፡
- በከተማው እስከ ወረዳ ድረስ የሚካሄደውን የበጀት ድልደላ ቀመር በማዘጋጀት፣ ለሚመለከተው አካል ይልካል፡፡
