የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መስሪያ ቤቶች የህንፃ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው። ‎********

ሐሙስ ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም

‎ አሶሳ፣

‎የአሶሳ ከተማ አስተዳደር የሴክተር መስሪያ ቤቶች የህንፃ ግንባታ በተያዘለት የጊዜ ገደብ አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

‎በ175,683,274 ብር እየተገነባ ያለው ህንፃው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የግንባታው ሳይት መሃንዲስ የሆኑት ኢንጅነር ዳዊት አመኑ ገልፀዋል።

‎ግራውንድ ፕላስ 5 (G+5) የሆነው ይህ ህንፃ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ በኪራይ ቤት ውስጥ ያሉ በርካታ የከተማ አስተዳደሩ መስሪያ ቤቶችን ከኪራይ ቤት እንደሚያወጣ ይጠበቃል።

‎እስካሁን ባለው ዳታ እንደ ከተማ አስተዳደር 12 ሴክተር መስሪያ ቤቶች፣ወረዳ አንድ 10 መስሪያ ቤቶች እንዲሁም ወረዳ ሁለት በተመሳሳይ 10 መስሪያ ቤቶች በኪራይ ቤት ውስጥ እንደሚገኙ መረጃው ያመላክታል።

‎የአሶሳ ከተማ አስተዳደር በየዓመቱ ለአሶሳ ከተማ አስተዳደር መስሪያ ቤቶች 6,396,000፣ለወረዳ አንድ 2,846,000 እንዲሁም ለወረዳ ሁለት 4,065,120 ብር በአጠቃላይ 13,307,120 ብር የቤት ኪራይ ክፍያ እንደሚከፍል ይታወቃል።

የሴክተር መስሪያ ቤቶቹ ህንፃ ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ካፌ፣ሻወር፣ሽንት ቤት እና ሌሎች አገልግሎቶችንም ያካተተ ነው።

‎ይህ ህንፃ ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ለቤት ኪራይ ሲወጣ የነበረውን ክፍያ ከማስቀረቱም በላይ በርካታ ተቋማትን በአንድ ቦታ ጠቅለል አድርጎ ስለሚይዝ ለባለጉዳዮች ምቹ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *