News

‎የአሶሳ ከተማ አስ/ር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ጋር በመተባበር አዲስ በተሻሻሉ አዋጆች እና ደንብና መመሪያዎች ላይ ለሚመለከታቸው የውስጥ ሰራተኞች ግንዛቤ ሰጠ።

‎ቅዳሜ መጋቢት 26/2018 ዓ.ም

‎አሶሳ፣

‎የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ልማት መምሪያ ሠራተኞቹን ከአዳዲስ አዋጆች እንዲሁም ደንብና መመሪያዎች ጋር የተገናዘቡ እንዲሆን በማሰብ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፍይናንስ ቢሮ ጋር በመተባበር መጋቢት 25/2018 ዓ.ም ለመምሪያው ሰራተኞች ስልጠና ሰጥቷል።

‎ስልጠናው በዋናነት የተቋሙ ሠራተኞች አዲስ በተሻሻሉ አዋጆች፣ደንቦች እና መመሪያዎች ላይ ጥሩ ግንዛቤ ኖሯቸው በዚሁ አግባብ ተገልጋዮችን እንዲያስተናግዱ ያለመ ነው።

‎ስልጠናውን የሰጡት ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች ስልጠና እንዲሰጡ ሲጠየቁ የመጀመሪያቸው እንደሆነ በመግለፅ ሌሎች ተቋማትም የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ልማት መምሪያን አርአያ ሊከተሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

‎የመምሪያው ኃላፊ ወ/ሮ ፋጡማ መሀመድ ተቋሙን በአዳዲስ አሰራሮች ለማስተሳሰር የሚያደርጉትን ጥረት ያደነቁት አሰልጣኞቹ ይህንን ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አደራ ብለዋል።

‎አሰልጣኞቹ አያይዘውም በየጊዜው አዳዲስ በሚወጡ አዋጆች፣ደንብና መመሪያ ተቋማት ሰራተኞቻቸውን በማሰልጠን በዚሁ አግባብ ባለጉዳዮችን ማስተናገድ እንደሚገባቸው ገልፀዋል።




Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *