News

የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን መሪ

ስነ-ምግባርና θረ-ሙስና የስራ ክፍል ተግባርና ሃላፊነት

ትምህርት መስጠት፦ ለተቋሙ ሠራተኞችና ለደንበኞች ስለ ሙስና አስከፊነት፣ ስለ ሥነ-ምግባር ምንነትና ስለ ፀረ-ሙስና ሕጎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ማዘጋጀት።

የሥነ-ምግባር ደንብ (Code of Conduct)፦ የተቋሙ የሥነ-ምግባር መመሪያዎች እንዲዘጋጁ፣ እንዲሻሻሉና ለሠራተኞች ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ።

5.1 የሙስና ተጋላጭነትን ማጥናት

ጥናትና ምርምር፦ በተቋሙ አሠራር ውስጥ ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ አሠራሮችን (ለምሳሌ፦ ግዢ፣ ቅጥር፣ የፋይናንስ ክፍያ) ማጥናትና መለየት።

የመፍትሄ ሃሳብ ማቅረብ፦ ለሙስና ቀዳዳ የሚሆኑ አሠራሮች እንዲደፈኑና የአሠራር ማሻሻያ (Business Process Re-engineering) እንዲደረግ ጥቆማ ማቅረብ።

5.2. የሀብት ምዝገባና ቁጥጥር ማድርግ

የሀብት ምዝገባ፦ የሕዝብ ተ῿ሚዎችና ሠራተኞች የሀብት ምዝገባ ሕጉ በሚጠይቀው መሠረት እንዲመዘገቡ ማስተባበርና መከታተል።

ጥቅም ግጭትን ማስወገድ፦ በሥራ ሂደት ውስጥ የግል ጥቅም እና የመንግሥት ሥራ የሚጋጩባቸውን ሁኔታዎች መከታተልና መከላከል (Conflict of Interest)።

5.3  ጥቆማዎችን መቀበልና መከታተል

ጥቆማ መቀበል፦ ስለ ሙስና ወይም ስለ ሥነ-ምግባር መጓደል የሚቀርቡ ጥቆማዎችን በሚስጥር መቀበልና ማደራጀት።

ቅድመ-ምርመራ፦ የቀረቡ ጥቆማዎች መነሻ ያላቸው መሆኑን በማጣራት ለሚመለከተው የሕግ አካል ወይም ለበላይ አመራር ሪፖርት ማቅረብ።

ጠቆሚዎችን መጠበቅ፦ ጥቆማ ያቀረቡ ግለሰቦች ጥቃት እንዳይደርስባቸው አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያገኙ መከታተል።

5.4 ክትትልና ሪፖርት ማቅረብ

የሥነ-ምግባር ክትትል፦ ሠራተኞች የተቋሙን የሥነ-ምግባር ደንብ አክብረው እየሰሩ መሆኑን መከታተል።

ሪፖርት፦ በየወቅቱ የተከናወኑ የፀረ-ሙስና ተግባራትን፣ የታዩ ድክመቶችንና የታረሙ የአሠራር ክፍተቶችን ለሚመለከተው አካል (ለፀረ-ሙስና ኮሚሽን ወይም ለተቋሙ መሪ) ሪፖርት ማድረግ።