News

የፕላን ትግበራ:በጀት ዝግጅት:ክትትልና ግምገማ ቡድን መሪ

 የፕላን ትግበራ:በጀት ዝግጅት:ክትትልና ግምገማ ቡድን መሪ ተግባር ሃላፊነት

የከተማዉን የልማት ዕቅድና ስትራቴጂ ላይ የተመሰረተና በከተማ አስተዳደሩ የሚፈጸም የረዥም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ የልማት እቅድ ያዘጋጃል፣ ሲጸድቅም ተግባራዊነቱን ይከታተላል፡፡

  • ከሚመለከታቸው የከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በረዥም በመካከለኛና በአጭር ጊዜ ዕቅዶች ውስጥ የሚንፀባረቁ በከተማ አስተዳደር የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች እንዲጠኑና እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ይከታተላል፣ ይገመግማል፡፡
  • የየሴክተሩን እቅድ አፈጻጸም እየተከታተለና  እየገመገመ የተቀነባበረ ሪፖርት በየሶስት ወሩ ለከተማ አስ/ር መንግስት ካቢኔ  ያቀርባል፣
  • የከተማ አስተዳደር አካላት የክልሉን የፋይናንስ ፖሊሲዎችን፣ህጐችን፣ደንቦችንና መመሪያዎችን ተከትለው መሰራታቸውን ይከታተላል ይቆጣጠራል፣
  • ከተማ አስተዳደሩ የፋይናንስ ክንውን ይዞታና አስተዳደር የሚያስረዳ ጠቅላላ  መግለጫ በየ 6 ወሩ ለከተማ አስተዳደር ካቢኔ ያቀርባል፡፡ ለአመቱ ከተዘጋጀው በጀት ሌላ ተጨማሪ በጀት  ሲገኝና በተገቢው አካል ሲፈቀድ  አዘጋጅቶ ያቀርባል፡፡ስለ ከተማዉ የፋይናንስ አያያዝና አጠቃቀም ጥናት እያደረገ የመፍትሄ ሃሳብ ያመነጫል፣
  • የከተማ አስተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶችና ሁለቱን ወረዳዎች ጨምሮ  የሚቀርቡትን መደበኛና የካፒታል በጀት ትክክለኛነት እየመረመረ ዓመታዊ በጀት አጠቃሎ በማዘጋጀት ለከተማ አስተዳድር ም/ቤት ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ያስተዳድራል፡፡
  • የከተማ አስተዳድሩን  መ/ቤቶች ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ መሰረት በማድረግ እንድተገብሩ ያደርጋል ፣ ተግባራዊነቱንም ይቆጣጠራል፡፡
  • የከተማውን ህዝብ ልማት በበላይነት ይመራል፣ያስተባብራል፣ይከታተላል፣ ይገመግማል፡፡
  • በክልሉ ገ/ኢ/ል/ቢሮ አማካኝነት ለከተማ አስ/ሩ ውስጥ ለመሥራት ፍላጐት ላላቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና  አስፈላጊውን ትብብር በማድረግና መረጃ በማቅረብ እንዲሁም የሚያቀርቡትን የልማት ዕቅድ በማቀድ ያስተባብርል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ ይገመግማል፡፡
  • በከተማው እስከ ወረዳ ድረስ የሚካሄደውን የበጀት ድልደላ ቀመር በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል ይልካል፡፡