በኮሪደር ልማት ውበቷ የደመቀው አሶሳ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዋና ከተማ የሆነቸው አሶሳ ከተማ ከጊዜ ወደ ጊዜ ውበቷ እየጨመረ፣ ለኑሮ እና ለሥራ ምቹ እየሆነች መጥታለች፡፡

የዚህ ዋነኛ ምክንያት ደግሞ ከተማዋ ቀን እና ሌሊት እያከናወነችው ያለው የኮሪደር ልማት ኢኒሼቲቭ ነው፡፡

የኅብረ ሔራዊነት ምሳሌ እና የብሔር ብሔረሰቦች መናገሻ የሆነችው አሶሳ ከተማ፤ ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በቅርብ ርቀት ላይም ትገኛለች፡፡

በከተማዋ በመጀመሪያው ምዕራፍ 9.6 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት የተከናወነ ሲሆን፣ በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ 15 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ገብረሚካዔል ጉድሬ ይገልጻሉ፡፡

የኮሪደር ልማቱ ከአሶሳ ከተማ አልፎ በተለያዩ የክልሉ ዞኖች እና ወረዳዎችም በመስፋፋት ላይ መሆኑንም ኃላፊው አክለው ገልጸዋል፡፡

የኮሪደር ልማቱ አካል የሆኑ አምስት የመዝናኛ ማዕከላትም ለነዋሪዎች ሁነኛ የመዝናኛ አማራጭ ሆነዋል፡፡ የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎችም በከተማዋ ፈጣን እድገት እና ውበት መደሰታቸውን መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *