News

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተግባርና ሃላፊነት

የኔትወርክ ዝርጋታ፦ የውስጥ መስመር (LAN) እና የውጪ መስመር (WAN) ዝርጋታዎችን ማከናወንና በትክክል መስራታቸውን ማረጋገጥ።

ሰርቨር ማስተዳደር፦ የተቋሙን ሰርቨሮች (Servers) መጫን፣ ማዋቀርና (Configuration) ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጡ ክትትል ማድረግ።

ኢንተርኔት፦ የኢንተርኔት አገልግሎት በሁሉም የሥራ ክፍሎች ያለምንም መቆራረጥ መኖሩን ማረጋገጥ።

6.1 የሃርድዌርና ሶፍትዌር ጥገና ማካሄድ

ጥገናና ክትትል፦ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ስካነሮችና ሌሎች የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች ሲበላሹ መጠገንና ወቅታዊ ምርመራ (Maintenance) ማድረግ።

ሶፍትዌር መጫን፦ ለሥራ የሚያስፈልጉ ሲስተሞችንና አፕሊኬሽኖችን መጫን፣ ማዘመን (Update) እና ፍቃዳቸውን (License) መቆጣጠር።

6.2 የመረጃ ደህንነትና ጥበቃ (Cybersecurity) ማድርግ

ደህንነት መጠበቅ፦ ተቋሙ ለሳይበር ጥቃት እንዳይጋለጥ ፋየርዎል (Firewall) እና አንቲ-ቫይረስ መጠቀም።

ባክአፕ (Backup)፦ ጠቃሚ መረጃዎች በድንገት ቢጠፉ እንኳ መልሶ ለማግኘት እንዲቻል በየጊዜው የመረጃ ቅጂ (Backup) መያዝ።

ሚስጥራዊነት፦ የተቋሙ መረጃዎች ካልተፈቀደላቸው አካላት መጠበቃቸውን ማረጋገጥ።

6.3 ሲስተም ማበልጸግና ማስተዳደር

ድረ-ገጽና ዳታቤዝ፦ የተቋሙን ድረ-ገጽ ማበልጸግ ወይም ማስተዳደር፤ እንዲሁም የደንበኞችንና የሠራተኞችን መረጃ የያዘ የዳታቤዝ ሥርዓት መገንባት።

አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች፦ ለተቋሙ ሥራ ቅልጥፍና የሚረዱ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ማጥናትና እንዲተገበሩ ሃሳብ ማቅረብ።

6.4 የቴክኒክ ድጋፍና ስልጠና መስጠት

Helpdesk፦ ሠራተኞች የቴክኖሎጂ መሣሪያዎችን ሲጠቀሙ ለሚያጋጥሟቸው ችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ መስጠት።

ስልጠና፦ ሠራተኞች አዳዲስ ሲስተሞችንና መሣሪያዎችን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው ስልጠናና ገለጻ መስጠት።