የመምሪያዉ ተግባርና ኃላፊነት

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ሰልጣንና ተግባራቸዉን እንደገና ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 94/2003 መሠረት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የተሰጠዉ ተግባርና ኃላፊነት እንደሚከተለዉ ቀርቧል፡፡

  1. የከተማዉን የልማት ዕቅድና ስትራቴጂ ላይ የተመሰረተና በከተማ አስተዳደሩ የሚፈጸም የረዥም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ የልማት እቅድ ያዘጋጃል፣ ሲጸድቅም ተግባራዊነቱን ይከታተላል፡፡
  2. ከሚመለከታቸው የከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በረዥም በመካከለኛና በአጭር ጊዜ ዕቅዶች ውስጥ የሚንፀባረቁ በከተማ አስተዳደር የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች እንዲጠኑና እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ይከታተላል፣ ይገመግማል፡፡
  3. የየሴክተሩን እቅድ አፈጻጸም እየተከታተለና  እየገመገመ የተቀነባበረ ሪፖርት በየሶስት ወሩ ለከተማ አስ/ር መንግስት ካቢኔ  ያቀርባል፣
  4. የከተማ አስተዳደር አካላት የክልሉን የፋይናንስ ፖሊሲዎችን፣ህጐችን፣ደንቦችንና መመሪያዎችን ተከትለው መሰራታቸውን ይከታተላል ይቆጣጠራል፣
  5. ከተማ አስተዳደሩ የፋይናንስ ክንውን ይዞታና አስተዳደር የሚያስረዳ ጠቅላላ መግለጫ በየ 6 ወሩ ለከተማ አስተዳደር ካቢኔ ያቀርባል፡፡ ለአመቱ ከተዘጋጀው በጀት ሌላ ተጨማሪ በጀት  ሲገኝና በተገቢው አካል ሲፈቀድ  አዘጋጅቶ ያቀርባል፡፡
  6. ስለ ከተማዉ የፋይናንስ አያያዝና አጠቃቀም ጥናት እያደረገ የመፍትሄ ሃሳብ ያመነጫል፣
  7. የከተማ አስተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶችና ሁለቱን ወረዳዎች ጨምሮ  የሚቀርቡትን መደበኛና የካፒታል በጀት ትክክለኛነት እየመረመረ ዓመታዊ በጀት አጠቃሎ በማዘጋጀት ለከተማ አስተዳድር ም/ቤት ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ያስተዳድራል፡፡
  8. የከተማ አስተዳድሩን  መ/ቤቶች ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ መሰረት በማድረግ እንድተገብሩ ያደርጋል ፣ ተግባራዊነቱንም ይቆጣጠራል፡፡
  9. የከተማውን ህዝብ ልማት በበላይነት ይመራል፣ያስተባብራል፣ይከታተላል፣ ይገመግማል፡፡
  10. በክልሉ ገ/ኢ/ል/ቢሮ አማካኝነት ለከተማ አስ/ሩ ውስጥ ለመሥራት ፍላጐት ላላቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግና መረጃ በማቅረብ እንዲሁም የሚያቀርቡትን የልማት ዕቅድ በማቀድ ያስተባብርል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ ይገመግማል፡፡
  11. በከተማው እስከ ወረዳ ድረስ የሚካሄደውን የበጀት ድልደላ ቀመር በማዘጋጀት፣ ለሚመለከተው አካል ይልካል፡፡