የመምሪያው ራዕይ፡ተልዕኮ እና እሴቶች

ራዕይ

በ2022 ዓ.ም የከተማችን ሕብረተሰብ ክፍል ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ልማት ተጠቃሚ ሆኖ ማየት ፡፡

ተልዕኮ

የከተማዉን የመረጃ ስርዓት በመዘርጋት ልማትን በተሻለ ዕቅድ በመምራት የሀብት ምንጭ በማሳደግ የመንግስትን ፋይናንስ በማስተዳደር የክትትልና ቁጥጥር ስርዓት በተሻለ ደረጃ በመዘርጋት ቀጣይነት ያለው ልማት እንድመጣ ማድረግ ፤

እሴቶች

የከተማ አስ/ሩ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በአዋጅ የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነቶች በብቃት ከመወጣትና በከተማዉ ዘላቂ ልማትን ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ሊያበረክት የሚገባውን አስተዋፅኦ በሚገባ ከማበረከት አንፃር በሥራ ሂደቱ አፈፃፀምም ሆነ በሠራተኞቹ የሥራ ዲሲፕሊን ዙሪያ የእለት ከእለት ተግባሩ በሚከተሉት የአሠራር መርሆዎችና እሴቶች ላይ የተመሠረተ ነው፡፡

  • ትኩረት ለተገልጋይ እርካታ
  • ሁል ጊዜ በዕቅድ መመራት
  • የቡድን ሥራ ለግብ ስኬት
  • ለዉጥ ለጋራ ተጠቃሚነት
  • ቁጠባ ለልማት
  • የስራ ተነሳሽነት መለያችን