News

ስለ እኛ

የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የበላይ ኃላፊዎች የፋይናንስ ኃላፊነቶች

  1. አጠቃላይ
  • የመምራትና የመወከል ኃላፊነት፦ የበላይ ኃላፊዎች የመስሪያ ቤታቸውን ሥልጣንና ኃላፊነት በመወጣት፣ የፀደቀውን በጀት መሠረት በማድረግ ወጪዎችን በመፈጸም፣ ፕሮግራሞችና ሕጎችን በማስፈጸም ረገድ ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው ።
  • ተጠያቂነትን ማረጋገጥ፦ የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ፣ ደንብና መመሪያዎች በመስሪያ ቤቱ ውስጥ በተሟላና ተገቢ በሆነ መንገድ ሥራ ላይ መዋላቸውን የማረጋገጥ ተጠያቂነት አለባቸው ።
  • ሥርዓት መዘርጋት፦ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ ግልጽነትና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓት የመዘርጋት ኃላፊነት አለባቸው ።
  • የበጀት ቁጥጥር፦ በየወጪ መደቡ ከተፈቀደው በጀት በላይ ወጪ ተደርጎ ክፍያ እንዳይፈፀም ጥንቃቄ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው ።
  • የንብረትና የሂሣብ አያያዝ፦ በደንቡና በመመሪያው መሠረት አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶች እንዲወገዱ እና ሊሰበሰቡ የማይችሉ ሂሣቦች ከመዝገብ እንዲሰረዙ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው ።